ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ
Tsehay Insurance S.C.

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ለማከናወን እንዲቻል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር ኤስአይቢ/63/2026 እና ኤስአይቢ/48/2019 እንዲሁም የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ አሰራር ደንብ መሰረት የቦርድ አባላት የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ በኩባንያው የባለአክሲዮኖች 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም መመረጡ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት የተሰየመው የቦርድ አባላት የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባላትን ጥቆማ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፤ እንዲሁም በኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የአሰራር ደንብ መሰረት ከሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ብቻ የሚቀበል ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ዕጩ የቦርድ አባላትን እንድትጠቁሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

1. የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮን የሆነ፤
2. የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
3. በሌላ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ፤
4. ዕድሜ 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
5. የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ፤ የኩባንያው ወይም ሌላ መድን ሰጭ ኩባንያ ሰራተኛ ያልሆነ፤
6. የትምህርት ደረጃ፡- ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ያጠናቀቀ፤ እንዲሁም በኢንሹራንስ፤ በሪስክ ማኔጅመንት፤ በፋይናንስ፤ በአካውንቲንግ፤ በማኔጅመንት፤ በኢኮኖሚክስ፤ በህግ፤ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፤ በኦዲቲንግ፤ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ፤ በኢንቨስትመንትና ዘላቂነት ወይም ተዛማጅ መስኮች የሙያ ዘርፍ የተመረቁ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስብጥር እንዲኖር ይበረታታል፤

7. የስራ ልምድ፡- ቢያንስ አምስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው፤ እንዲሁም በቢዝነስ አስተዳደር በይበልጥም በኢንሹራንስ ዘርፍ በቂ የስራ ልምድ ያለው፤ ወይንም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ከተመረጠ በኋላ በኢንሹራንስ ቢዝነስ ማኔጅመንት፤ በኮርፖሬት አስተዳደር፤ በፋይናንስ አናሊሲስ፤ በሪስክ ማኔጅመንት፤ ዘርፉን በሚመለከት በወጡ የህግ ማዕቀፎች፤ደንቦችና መመሪያዎች ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ ፤
8. የህግ ሰውነት ያለው ድርጅት በዕጩነት ሊጠቆም ይችላል፡፡የህግ ሰውነት ያለው ድርጅት ዕጩ ሲደረግ የህግ ሰውነት ያለውን ድርጅት በቦርድ የሚወክል የተፈጥሮ ሰው ዝርዝር መረጃ መገለጽ ይኖርበታል፡፡
9. በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ዉጭ የእምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈጸመ፤ ለገንዘብ ተቋማትና ለተቆጣጣሪ አካል ሃሰተኛ መረጃ ያልሰጠ፤ የስነ-ምግባር ደንቦችን ባለማክበር የስነ-ሥርዓት እርምጃ ያልተወሰደበት፤ በሙስና ወንጀል ተከሶ ያልተፈረደበትና የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ያልተገደበ፤
10. የፋይናንሻል ጤናማነትን (Financial soundness) መስፈርት የሚያሟላ፤

ማሳሰቢያ

1. በወንድ ፆታ የተገለጸው ለሴት ፆታም ይውላል፡፡
2. ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር ኤስአይቢ /63/2026 መሰረት በቦርዱ ቢያንስ ሁለት ሴት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እንዲኖሩ ስለሚደነግግ ባለአክሲዮኖች ይህንን አውቃችሁ ጥቆማውን እንድታደርጉ ኮሚቴው ያሳስባል፡፡
3. ጥቆማ የሚደረግበትን ቅጽ አዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት፤ በሁሉም የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ቅርንጫፎች፤ እንዲሁም ከኩባንያው ድረ-ገጽ www.tsehayinsurance.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
4. የተሞላው የጥቆማ ቅጽ አዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ፤ በሁሉም የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ቅርንጫፎች፤ ወይም በኢሜል አድራሻ tsehayinsurancesc@gmail.com መጠቆም ይቻላል፡፡
5. ከጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ከወዲሁ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
6. ለጥያቄና ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመቅረብ፤ በኢሜል አድራሻ:tsehayinsurancesc@gmail.com ወይም በስልክ ቁጥር +251116506630 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

***የፀሐይ ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ***

የመጠቆሚያ ፎርሙን ከስር ባለው ሊንክ ያገኙታል