ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ታማኝ የግብር ከፋይ በመሆኑ ተሸለመ

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ታማኝ የግብር ከፋይ በመሆኑ ተሸለመ

መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በ7ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና መርሃ ግብር ላይ ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. የሚጠበቀበትን ግብር በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈሉ ምክንያት የብር ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል። ኩባንያው ከሚሰጠው አስተማማኝ የጠቅላላ እና የሕይወት የመድን ሽፋን አገልግሎት በተጨማሪ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ብሎም ያለበትን ማህበራዊ ሀላፊነት የበኩሉን ደርሻ በሚገባ እየተወጣ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ያገኘው ሽልማት ማሳያ ነው፡፡ ተቋሙን ለዚህም ሽልማት ያበቁት ውድ ደንበኞቹ፣ ባለአክሲዮኖች፣ የስራ አመራር ቦርድ አባላት እና ታታሪ ስራተኞቹ ናቸው፡፡ ወደፊትም መሰል የኩባንያውን ግዴታዎችን የመወጣት ኃላፊነት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ሲገልጽ በደስታ ነው።

ፀሐይ ለሁሉም ታበራለች!