The Sun Shines For All! ፀሐይ ለሁሉም ታበራለች!

የባለአክሲዮኖች 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ

Tsehay Insurance S.C

ለፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር በንግድ ምዝገባ ቁጥር MT/AA/3/0017159/2004 የተመዘገበ፤ በጠቅላላ እና በህይወት መድን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የተሰማራ፤ የተከፈለ ካፒታሉ ብር 350.49 ሚሊዮን የሆነ፤ ዋናው መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ፤- አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 2185 ሲሆን፤

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 366(1) ፣ 367፣ 393፣ 394 መሰረት የፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 230 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ሆቴል ቁጥር 1 ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የኩባንያዉ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው፤ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በቦታዉ ተገኝተዉ እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪዉን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡

የባለአክሲዮኖች 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣

2. እ.ኤ.አ በ2022/2023 በጀት ዓመት የተሸጡ አዳዲስ አክሲዮኖችንና የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ እና አዲስ ባለአክሲዮን መቀበል፤

3. እ.ኤ.አ. የ2022/2023 በጀት ዓመትን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤

4. እ.ኤ.አ. የ2022/2023 በጀት ዓመትን የዉጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤

5. በዘመኑ የተጣራ የትርፍ አደላደል እና አከፋፈልን በሚመለከት ተወያይቶ መወሰን፤

6. እ.ኤ.አ ከ2023/2024 የዉጭ ኦዲተሮችን የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፤

7. እ.ኤ.አ የ2022/2023 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ከተጣራ የትርፍ ድርሻ የሚታሰብ ክፍያን እና እ.ኤ.አ የ2023/2024 በጀት ዓመት ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን፤

8. ህጋዊ ሰውነት ባለው ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ዉክልና የተተኩና በማገልገል ላይ ያሉ የቦርድ አባላትን ሹመት ማሳወቅ እና ማጽደቅ፤

9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴን ሪፖርት ማድመጥ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፤

10. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

1. ማንኛውም ባለአክሲዮን ለስብሰባው ሲመጣ ማንነታቸዉን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናዉንና ቅጅዉን ይዘዉ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

2. በአካል ጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች፡-

• ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ ከብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 201/202 ከስብሰባው ሶስት ቀናት በፊት ቀርበው የውክልና ቅፅ በመሙላት በወኪሎቻቸው አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ወይም፤

• አግባብነት ካለው አካል ተመዝግቦ የተረጋገጠ ህጋዊ የውክልና ስልጣን በተሰጣቸው ወኪሎቻቸው አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ተወካዮች፤ አግባብነት ካለው ህጋዊ አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የወካዮቻቸውን መታወቂያ ኮፒ እና የራሳቸውን መታወቂያ ኦሪጅናልና ኮፒ፤ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ.0116506630/38 ይደውሉ

የፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

Head Office Address

Bole Bridge, In front of Brass Hospital
Tel:+251- 111-11 97 70/71
Office:+251 - 116- 50 66 32/37/38
Fax: +251-111-11 98 86
Web: www.tsehayinsurance.com
E-mail: officemail@tsehayinsurance.com
P.O.Box: 56144

Quick Links

Products & Sevices

Newsletter

Subscribe our newsletter
to get latest updates