የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባው የሚካሄድበትን ቀን እና የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ለውጥን ለማሳወቅ የቀረበ ጥሪ

 

የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤን በተመለከተ አስቀድሞ የተደረገን የስብሰባ ጥሪ፤ ስብሰባው የሚካሄድበትን ቀን እና የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ለውጥን ለማሳወቅ የቀረበ ጥሪ!

ለፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪን በተመለከተ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣው ማስታወቂያ ጉባኤው የሚካሄድበት ቀን ኅዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2″30 ሰዓት ጀምሮ መሆኑን  እና የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ ከተማ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 03 ፤የቤት ቁጥር 2185 እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ሆኖም ግን ጉባኤው ታህሳስ 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2“30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሂልተን ሆቴል የሚካሄድ መሆኑን፤ እንዲሁም የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻም አክሲዮን ማህበሩ ወደ አስገነባው ህንጻ አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 05 ፤የቤት ቁጥር አዲስ የተዛወረ መሆኑን እያሳወቅን የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ማሳሰቢያ ፡–     

  • የጉባኤውን አጀንዳዎች እና ሌሎች መረጃዎችን የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪን በተመለከተ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣው ማስታወቂያ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
  • በጉባኤው ላይ በራሳችሁ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች፤ ተወካዮቻችሁን ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የዉክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሶስት ቀን በፊት አዲስ አበባ ከአራዳ ጊወርጊስ ወደ ስድስት ኪሎ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ደጃች ዉቤ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 4ኛ ወለል ላይ በማህበሩ ፀሐፊ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የዉክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የዉክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ.0116506630 መደወል ይችላሉ፡፡

የፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ!