የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ
የስብሰባ ጥሪ
ለፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ


በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 366(1) ፣367(1) እና 370፤ እንዲሁም በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 12 መሰረት የፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ኅዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 230 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሂልተን ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች

  • 1.1. የአክሲዮን ማህበሩ ስም                                      –  ፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር
  • 1.2. የአክሲዮን ማህበሩ አይነት                                  – በጠቅላላ እና በህይወት መድን ስራዎች የተሰማራ፤
  • 1.3 የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) –   ብር 500,000,000
  • 1.4 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)   –  ብር 500,000,000
  • 1.5 የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር                         –  MT/AA/3/0017159/2004
  • 1.6 የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ            – አዲስ አበባ ከተማ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 03 ፤የቤት ቁጥር 2185
  • 1.7 የአክሲዮን ማህበሩ ድረ-ገጽ                                  – www.tsehayinsurance.com

2. የባለአክሲዮኖች 15ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፤

2.1 እ.ኤ.አ. የ2025/2026 በጀት ዓመትን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
2.2 እ.ኤ.አ. የ2025/2026 በጀት ዓመትን የዉጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
2.3 እ.ኤ.አ. የ2025/2026 በጀት ዓመት በተገኘ የተጣራ የትርፍ አደላደል እና አከፋፈልን በሚመለከት ተወያይቶ መወሰን፤
2.4 እ.ኤ.አ የ2025/2026 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ከተጣራ የትርፍ ድርሻ የሚታሰብ ክፍያን እና እ.ኤ.አ የ2026/2027 በጀት ዓመት ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን፤
2.5 የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴን ሪፖርት ማድመጥ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ማካሄድ፤


3. የባለአክሲዮኖች 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፤
3.1 የማህበሩን መመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፤
ማሳሰቢያ ፡-
• በጉባኤው ላይ በራሳችሁ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች፤ ተወካዮቻችሁን ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የዉክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሶስት ቀን በፊት አዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 201/202 በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የዉክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የዉክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
• የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ፤ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናዉንና ኮፒ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ የዉጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ.0116506630 መደወል ይችላሉ፡፡
የፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ!